ህትመቶች

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን በውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ዙሪያ የደንበኞች መብት፣ኃላፊነትና ተጠያቂነት መመሪያ ቁጥር 5/2012

image description

ባለስልጣኑ የከተማውን ነዋሪ የውሃ አቅርቦት እና የፍሳሽ አገልግሎት ፍላጎት የማርካት እና አሰራሩን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ ፍትሃዊ እና ከኪራይ ሰብሳቢነት የፀዳ ለማድረግ የደንበኞች አገልግሎቱን ለማግኘት ሟሟላት ያለባቸውን ቅዴመ ሁኔታዎች በማስቀመጥ እና ስራዎች የሚከናወኑበትን ስታንዳርድ በማውጣት ዘርፈ ብዙ ስራዎችን እያከናወነ የሚገኝ በመሆኑ፤ ይህም የባለስልጣኑ አሊማ ግቡን ይመታ ዘንዴ የደንበኞችን መብት፣ ተግባር እና ሃሊፊነት በግልፅ ለይቶ ማስቀመጥ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤ የባለስልጣኑ ከደንበኞቹ ጋር ያለው አስተዳደራዊ እና ኦፕሬሽናል ግንኙነት ግልፅ ፣ተገማች እና ወጥነት ያለው እንዱሆን በማስፈለጉ፤ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግልት አካላት እንደገና ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 35/2004 አንቀጽ 53 ንዑስ አንቀጽ 2 በተሰጠው ስልጣን መሠረት ይህንን መመሪያ አውጥቷል፡፡