ህትመቶች

162/2016 የተሻሻለ የከተማ መሬት ሊዝ_ደንብ

image description

መሬት ለአንድ ሀገር ማኀበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ወሳኝ የሆነ ሀብት እንደመሆኑ መጠን መንግሥት ይህንን ውስን ሀብት ፍትሐዊ፣ ግልጽ እና ተጠያቂነትን ባሰፈነ አሠራር ጥቅም ላይ መዋሉን ማረጋገጥ የሚያስፈልግ በመሆኑ፤ የከተማ አስተዳደሩን የልማትና መልካም አስተዳደር ችግሮች መፍታት የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ እና ግልጽ የአሰራር ሥርዓት በመዘርጋት በመሬት ልማትና አስተዳደር ዘርፍ የሚስተዋሉ የአሰራርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እልባት መስጠት በማስፈለጉ፤ የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ በማጥናት ወደ ሥራ የተገባ በመሆኑ አገልግሎት እየተሰጠባቸው የሚገኙት ደንብና መመሪያዎች ከተደረጉት የአደረጃጀት ለውጦች ጋር የተናበቡ መሆን ስላለባቸውና የከተማው ዕድገትን ተከትሎ የመጣ የልማት ፍላጎት እድገት በመኖሩ፤ በአገልግሎት አሰጣጥ ሥራ ላይ ላጋጠሙ የአሰራር ችግሮች መፍትሔ መስጠት በማስፈለጉ፤በሥራ ላይ በነበሩ ህጎች ላይ የሚስተዋሉ የተናባቢነትና የግልጸኝነት ችግሮች እና ህዝቡ የሚያነሳቸው የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን መልስ ለመስጠት እና በውሳኔ አሰጣጥ እንዲሁም በአፈጻጸም ሂደት በደንብ እና መመሪያዎች ላይ ላጋጠሙ ችግሮች የማብራሪያና ሰርኩላሮች መብዛት እርስ በራስ የሚጋጩ ውሳኔዎችን ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ግልጽና ወጥ የሆነ የሊዝ ደንብ ማሻሻል አስፈላጊ በመሆኑ፤