ህትመቶች

164/2016 የነገዋ የሴቶች ተሀድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል

image description

በተሻሻለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቻርተር አዋጅ ቁጥር 01/1ሺ0-5 (እንደተሻሻለ) አንቀጽ  ንዑስ አንቀጽ (5) መሠረት የነዋሪዎች ደህንነትና ምቾት የተጠበቀበት በተለይም ሴቶች የተለየ ድጋፍ የሚያገኙበት ከተማ ማድረግ ለከተማው አስተዳደር በዓላማ ደረጃ የተደነገገ በመሆኑ፤ ለጎዳና ህይወት፣ ለወሲብ ጥቃት፣ ለወሲብ ንግድ እና ተመሳሳይነት ላላቸው ማህበራዊ ችግር የተጋለጡ ሴቶችን ከችግር በማውጣት አማራጭ የገቢ ማስገኛ ሥራ ላይ መሰማራት እንዲችሉ የሚያበቃቸውን የክህሎት፣ የሥነ-ምግባር፣ የሥራ ባህል እና የሥራ እድል እንዲፈጠርላቸው በማድረግ የወደፊት ተስፋቸው ብርሃን የሞላበት እንዲሆን ለማድረግ የሴቶች ተሃድሶና ክሎት ማበልጸጊያ ማዕከል ማቋቋም በማስፈለጉ፤ማዕከሉን በተለይም ለጎዳና ህይወት፣ የፆታዊ ጥቃት ሰለባና ለወሲብ ንግድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴቶች መጠጊያ፣ መጠለያ፣ ማገገሚያና የተመሰቃቀለ ህይወታቸውን እንደገና ለማስተካከል የሙያና ክህሎት ሥልጠናዎች የሚያገኙበትን እና በዘላቂነት እንዲቋቋሙ የሚያግዝ አቅም ያለው ራሱን ችሎ ተግባሩን የሚያከናውን ማዕከል እንዲሆን ለማስቻል፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ,4/2ሺ%6 አንቀጽ - በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡