ደንብ ቁጥር 170/2016 የኅብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀትና አሰራር ደንብ
ደንብ ቁጥር፻፸/፪፻፲፮ የኅብረት ሥራ ማህበራት አደረጃጀትና አሰራር ደንብ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረት ሥራ ኮሚሽን ቀደም ሲል በተለያዩ የኅብረት ሥራ ማህበራት ዓይነቶች የተደራጁ ማህበራትን ውጥታማነት ለማረጋገጥ የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የህብረት ሥራ ማህበራቱን ለመደገፍ፣ ለመከታተልና ለመቆጣጠር የወጡ በርካታ መመሪያዎችን ወደ አንድ ሰብሰብ በማድረግ ለአፈጻጸም ምቹ፣ ግልጽ እና ለሕብረት ሥራ ማህበር አባላት በቀላሉ ተደራሽ መሆን የሚችል ደንብ አድርጎ ማውጣቱ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ,4/፪፻፲፮ አንቀጽ -4 መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡