ደንብ ቁጥር 171/2016 የኀብረት ሥራ ማኀበራት የግዥና ንብረት አስተዳደር አሠራር ደንብ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኅብረት ሥራ ማህበራት አዋጅን ለማስፈጸም፣ የኅብረት ሥራ ማህበራትን ለመምራት፣ ለመቆጣጠር፣ በውጤታማነት እንዲሰሩ፣ በከተማው አስተዳደር የተደረገላቸውን ድጋፍ ለታለመለት ዓላማ ማዋላቸውን ለመከታተል የሚያስችልና የሚመሩበት የአሰራር ሥርዓት በሕግ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር 94/2ሺ16 አንቀጽ 84 መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡