ደንብ ቁጥር 178/2016 በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ባለሙያዎች የደንብ ልብስ አለባበስ

በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ውስጥ ለሚሰሩ ባለሙያዎች ወጥ የሆነ የአለባበስ፤ የጌጣጌጥ እና የመዋቢያ አጠቃቀም ሥርዓት በመዘርጋት የሀገር ባልህና እሴት እንዲጠበቅ ለማድረግና በዘርፉ ተሰማርተው የሚሰሩ
ሙያተኞች ሊደርስባቸው ከሚችለው አካላዊ፤ ሥነ-ልቦናዊ ጫና እና አላስፈላጊ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ዓለም አቀፍ መስፈርትን የሚያሟላ እንዲሆን ማድረግ በማስፈለጉ፤ በከተማችን በሆቴልና መሰል አገልግሎት ሰጪ
ተቋማት ወጥ የሆነ የአለባበስ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር
፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀፅ ፺፭ መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡