ደንብ ቁጥር 161/2016 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የማህበራዊ ኃላፊነት አሰራርን ለመደንገግ የወጣ ደንብ

የከተማ አስተዳደሩ በከተማዋ ዘላቂ ልማትና ዕድገት ለማምጣት ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጎን ለጎን የከተማው ነዋሪ ህብረተሰብ በግልም ሆነ በተደራጀ ሁኔታ ሀብቱንና ዕውቀቱን በማቀናጀት የከተማዋን ማህበራዊና
ኢኮኖሚያዊ ችግሮች በመቅረፍና የህዝቡን ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሂደት ተሳታፊ በመሆን ድርሻውን መወጣት እንዲችል ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር በማስፈለጉ፤ በአዲስ አበባ ከተማ የማህበራዊ ኃላፊነት፣ የማህበራዊ
አገልግሎትና የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጥ በተደራጀና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት የሚያስችል የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በተለያየ የሙያ መስክ የተሰማሩ ግለሰቦች፤ ባለሀብቶች፤
ተማሪዎች የከተማዋን ዘላቂ ልማትና ዕድገት ለማምጣት በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ተሳታፊ በመሆን ማህበራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ ለማስቻል፤ የከተማው ነዋሪ በፈቃደኝነት እርስ በእርስ የመተሳሰብ የመደጋገፍና የመረዳዳት ባህል እንዲጎለብትና ዜጎች በአካባቢያቸው ጉዳይ ላይ በራሳቸው ተነሳሽነት የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻልና የእውቅናና የማበረታቻ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰንበወጣው አዋጅ ቁጥር, ፹፬/፪ሺ%6 አንቀፅ 1 መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡