ህትመቶች

182/2017 የመንግስት አገልግሎቶችን በውል በሶስተኛ ወገን ለማሠራት የወጣ ደንብ

image description

በከተማ አስተዳደሩ ውስጥ የሚገኙ የመንግስት ተቋማት ያለባቸውን የአገሌግሎት ጫና በመቀነስ ስትራቴጂክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ ማድረግ በማስፈለጉ፤ የመንግሥትን አገልግሎት ለህብረተሰቡ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ የተገልጋዩን እርካታ ለማሳደግ አገልግልቶቹን በውል በሶስተኛ ወገን ማሰራት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የመንግሥት አገልግሎት የሕዝብን ጥቅም በማይጎዳ መልኩ የተወሰኑ የሥራ መደቦችን ወይም ሥራዎችን ለግል ድርጅቶች ወይም ለሌሎች ተቋማት በውል ስለሚሻገርበት ሁኔታ ግልጽ የአሰራር ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና በመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀፅ ፺፬ መሰረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡