186/2017 የተርሚናል አገልግሎት አሰራርና ቁጥጥር ደንብ.pdf

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በትራንስፖርት ዘርፍ የከተማዋን እድገት ደረጃ የሚመጥን የተገልጋይን እርካታ ያረጋገጠ የባለድርሻ አካላት ሚና በአደረጃጀትና በአሰራር በመለየት ግልጽና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር በመዘርጋት በዘርፉ የሚፈጠር ሥራ እድልና ሀብት ክፍፍል ፍትሀዊነት በማረጋገጥ ተዋንያን ለአገልግሎት አሰጣጥ የሚኖራቸውን ተነሳሽነት በማሳደግ አገልግሎቱን ቀልጣፋ ማድረግ በማስፈለጉ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ የአዲስ አበባ ከተማ
አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀጽ ፺፭ በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ይህን ደንብ አውጥቷል፡፡