191_2017 የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ምክር ቤት እና የአደጋ ጊዜ ፈንድ ማቋቋሚያ ደንብ

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ፖሊሲን በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በውጤታማነት ለመተግበር እንዱሁም የተለያዩ ባድርሻ አካላትን የትብብር፤ የስርጸት፤ ቅንጅታዊ አሰራርና ተጠያቂነት እንዲኖር የሚያስችል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ምክር ቤት ማቋቋም አስፈሊጊ በመሆኑ፤በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ምክንያቶች አደጋዎች ሲከሰቱ የሚያስከትለት የሰው፣ የንብረት ብሎም የነዋሪ መፈናቀል ጉዳት የሚያስከትል በመሆኑ የጉዳቱ ሰለባ የከተማዋ ነዋሪዎችን መልሶ ለማቋቋም እጅግ ከፍተኛ ሀብት የሚጠይቅ በመሆኑ፤የአደጋ ዝግጁነትን በማረጋገጥ የአደጋ ተጎጂዎች የአሰቸኳይ ጊዜ የሰብዓዊ ዕርዲታና ደጋፌ፣ የመልሶ ግንባታ እና በዘላቂነት መልሶ ማቋቋም ሂደት የሚያስፈልግ ሀብት የማሰባሰብና የማስተዳደር የአፈጻጸም ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀፅ ፺፬ መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡