ህትመቶች

192_2017 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዳሪ ትምህርት ቤት

image description

በአዲስ አበባ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በመማር ላይ ከሚገኙት ወጣት ተማሪዎች መካከል የላቀ ውጤት ያላቸውን በመለየትና ወደ አዳሪ ትምህርት ቤት በማስገባት ተገቢውን ክትትልና ድጋፍ በማድረግ በክህሎታቸውና በእውቀታቸው የላቁ ተማሪዎችን በማፍራት ለሌሎች ተማሪዎች አርዓያ በመሆን በተማሪዎች መካከል የመነሳሳትና የውድድር መንፈስ እንዲፈጠር ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤የላቀ ውጤት ኖሯቸው ነገር ግን በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር ምክንያት ተገቢውን ድጋፍ የማያገኙትን በማገዝ እና ለትምህርት ጥራት መሻሻል የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ እናየዐይነ-ስውራን ልዩ የትምህርት ፍላጎቶችን ለማሟላት እና ሀገሪቱ የአካል ጉዳተኞች መብቶችን ለማክበር ያጸደቀቻቸውን ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን እና ፍትሃዊ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ አስፈላጊ ግብዓቶችን፣ የሰለጠኑ ባለሙያዎችን እና ተገቢ ሥርዓተ ትምህርት ያላቸው ተቋማትን ማቋቋም አስፈላጊ በመሆኑ፤ፈጣንና ከፍተኛ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በማወዳደርና በአዳሪ ትምህርት ቤቱ በማስገባት ተገቢውን ትምህርት፣ ክህሎት፣ አገልግሎት እና ድጋፍ በመስጠት ማስተማር ተማሪዎች ራሳቸውን ችለው፣ ለቤተሰባቸው ብሎም ለሃገራቸው ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ እና ሌሎችም ተማሪዎችና ትምህርት ቤቶች በአዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ውጤት ተነሳስተው በያሉበት ውጤታቸውንና የትምህርት ቤት ደረጃቸው ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋፅዖ ያለው በመሆኑ፤ውጤታማ ተማሪዎች እና በቂ የትምህርት እድሎችን በማመቻቸት ለአዳሪ ትምህርት ቤቱ እንዲሁም በአገር አቀፍ ደረጃ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ህይወት ውስጥ ሙሉ ተሳትፎ እና አስተዋፅዖ እንዲያበረክቱ ማድረግ አስፈላጊ ስለሆነ፤የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፹፬/፪ሺ፲፮ አንቀፅ ፺፫ ንዑስ አንቀጽ (፩) በተሰጠው ሥልጣን መሰረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡