ህትመቶች

197_2017 የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች የሚገኙ የአሰልጣኞች የዝውውርና የምደባ አፈጻጸም ደንብ

image description

የአሰልጣኝና ሰልጣኝ ቁጥር ለማጣጣም ዝውውር በመስራት ጥራቱን የጠበቀና ውጤታማ የስልጠና አሰጣጥ እውን ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በከተማ አስተዳደሩ ሥር የሚገኙ የመንግስት ቴክኒክና ሙያ ማሰልጠኛ ተቋም የሚሰጡ የስልጠና ዘርፎችን የአካባቢ የመልማት ጸጋን መሰረት አድርጎ በተጠኑ የስልጠና መስኮች ብቻ ስልጠናቸውን እንዲሰጡ ለማድረግ የዞኒግና ዲፈረንሼሽን ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ፤ የአዲስ አበባ ከተማ ካቢኔ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአስፈጻሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሰን በወጣው አዋጅ ቁጥር ,4/2ሺ%፮ አንቀጽ -4 መሠረት ይህንን ደንብ አውጥቷል፡፡